ሐዋርያት ሥራ 2:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል እንዲህ ተብሎ የተነገረ ነው፤

17. “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመጨረሻው ቀን፣መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ጒልማሶቻችሁ ራእይ ያያሉ፤ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ።

18. በዚያ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ፣መንፈሴን አፈሳለሁ፤እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።

ሐዋርያት ሥራ 2