ሉቃስ 1:78-80 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

78. ከአምላካችንም በጎ ምሕረት የተነሣ፣የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤

79. ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”

80. ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም ሕዝብ በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሓ ኖረ።

ሉቃስ 1