ሉቃስ 1:66-69 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

66. ይህንም የሰሙ ሁሉ፣ “ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ያዙ፤ የጌታ እጅ በርግጥ ከእርሱ ጋር ነበርና።

67. የሕፃኑም አባት ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤

68. “የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቶአልና።

69. በባሪያው በዳዊት ቤት፣የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤

ሉቃስ 1