6. ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ወደ አሦር ይወሰዳል፤ኤፍሬም ይዋረዳል፤እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።
7. ሰማርያና ንጉሥዋ፣በውሃ ላይ እንዳለ ኩበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።
8. የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤እሾኽና አሜኬላ ይበቅልባቸዋል፤መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤በዚያን ጊዜ ተራሮችን፣ “ሸፍኑን!”ኰረብታዎችንም፣ “ውደቁብን!” ይላሉ።
9. “እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤በዚያም ጸናችሁ፤በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ጦርነት አልጨረሳቸውምን?
10. በፈለግሁ ጊዜ እቀጣቸዋለሁ፤ስለ ድርብ ኀጢአታችሁም ይቀጧቸው ዘንድ፣በእነርሱ ላይ ይሰበሰባሉ፤