2 ዜና መዋዕል 7:20-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. በዚያን ጊዜ እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድሬ እነቅላቸዋለሁ፤ ለስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስ እተዋለሁ፤ በሕዝቦችም ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ አደርገዋለሁ።

21. ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም በአጠገቡ የሚያልፉ ሁሉ በመገረም፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያመጣው ከቶ ለምን ይሆን?’ ይላሉ፤

22. ሕዝቡም፣ ‘ይህን ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው፣ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፣ ስላመለኳቸውና ስላገለገሏቸው ነው’ ብለው ይመልሳሉ።”

2 ዜና መዋዕል 7