2 ዜና መዋዕል 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ።

2. እንዲሁም የጐኑ ስፋት ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ ክብ በርሜል ቀልጦ ከፈሰሰ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።

3. ከበርሜሉ ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኮርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኮርማዎቹም ከበርሜሉ ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።

2 ዜና መዋዕል 4