2 ዜና መዋዕል 17:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዛቱንም ተከተለ።

5. እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።

6. ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበር፤ እንደዚሁም ማምለኪያ ኰረብታዎችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ አስወገደ።

7. በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ሹማምቱን ማለትም ቤን ኀይልን፣ አብድያስን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያን ላካቸው።

2 ዜና መዋዕል 17