2 ዜና መዋዕል 13:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሰራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሰራዊት በስተ ጀርባ እንዲያደፍጡ ላከ፤ የቀረውም ሰራዊት ከእርሱ ጋር የይሁዳን ሰራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙ አደረገ።

14. የይሁዳም ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከታቸውን ነፉ።

15. የይሁዳም ሰዎች በፉከራ የጦርነት ድምፅ አሰሙ፤ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት ፊጽሞ መታቸው።

16. እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

2 ዜና መዋዕል 13