2 ነገሥት 9:29-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. አካዝያስ በይሁዳ የነገሠው፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት ነበር።

30. ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይኗን ተኳኵላ፣ ጠጒሯንም አሰማምራ በመስኮት ትመለከት ነበር።

31. ኢዩ የቅጥሩን በር አልፎ ሲገባ፣ “ጌታህን የገደልህ አንተ ዘምሪ የመጣኸው በሰላም ነውን?” ስትል ጠየቀችው።

32. ቀና ብሎ ወደ መስኮቱ ተመለከተና፣ “ማነህ አንተ? ማነው የሚተባበረኝ ሲል ጮኾ ተጣራ። ሁለት ሦስት ጃንደረቦችም ቊልቊል ወደ እርሱ ተመለከቱ፤

2 ነገሥት 9