2 ነገሥት 2:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ኤልሳዕ እንደ ተናገረውም ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ የተፈወሰ ነው።

23. ኤልሳዕም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድ ላይ ሲሄድ ሳለም ልጆች ከከተማ ወጥተው፣ “አንተ መላጣ፤ ውጣ!አንተ መላጣ ውጣ!” እያሉ አፌዙበት።

24. ኤልሳዕም ዘወር ብሎ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከዱር ወጥተው ከልጆቹ አርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው።

25. እርሱም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

2 ነገሥት 2