22. ለመሆኑ የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው?ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው?ዐይንህንስ በኵራት ያነሣኸው በማን ላይ ነው?በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እንዴ?
23. በመልእክተኞችህ አማካይነት፣በአምላክ ላይ የስድብ መዓት አውርደሃል፤እንዲህም ብለሃል፤“በብዙ ሠረገሎቼ፣የተራሮቹን ከፍታ፣የሊባኖስንም የመጨረሻ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ረጃጅም ዝግባዎቹን፣ምርጥ የሆኑ ጥዶቹንም ቈርጫለሁ፤ወደ ሩቅ ዳርቻዎቹ፣ወደ ውብ ደኖቹም ደርሻለሁ።”
24. “በሌሎች አገሮችም የውሃ ጒድጓዶች ቈፍሬአለሁ፤በዚያም ውሃ ጠጥቻለሁ፤በእግሬ ጫማዎችም፣የግብፅን ምንጮች ሁሉ ረግጬ አድርቄአለሁ።”
25. “ ‘ከብዙ ጊዜ በፊት፣ይህን እኔ እንዳደረግሁት አልሰማህም ነበርን?ዕቅዱን ገና ድሮ አውጥቼ፣አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።