6. እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው ሊገናኘን መጥቶ፣ ‘ወደ ላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ ሂዱና፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ ሰዎች የምትልከው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ከተኛህበት ዐልጋ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ።” ’
7. ንጉሡም፣ “ለመሆኑ ሊገናኛችሁ መጥቶ እንዲህ ያላችሁ ሰው እንዴት ያለ ነው?” ሲል ጠየቃቸው።
8. እነርሱም “ሰውየው ጠጒራም ልብስ የለበሰ ነው፤ በወገቡም ላይ ጠፍር ታጥቆአል” አሉት።ንጉሡም፣ “ዐወቅሁት፤ ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አላቸው።
9. ከዚያም ንጉሡ አንድ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ወታደሮቹ ጋር ወደ ኤልያስ ላከ። የአምሳ አለቃውም ኤልያስ ወደ ተቀመጠበት ኰረብታ ጫፍ ወጥቶ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ሰው፤ ንጉሡ፣ ‘ና ውረድ’ ይልሃል” አለው።