2 ቆሮንቶስ 5:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።

9. ስለዚህ በሥጋ ብንኖርም ወይም ከሥጋ ብንለይም ዐላማችን እርሱን ደስ ማሰኘት ነው።

10. ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና፤ እያንዳንዱም ሰው በሥጋው ለሠራው በጎ ወይም ክፉ ሥራ ተገቢውን ዋጋ ይቀበላል።

2 ቆሮንቶስ 5