2 ሳሙኤል 22:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤እርሱ ተቈጥቶአልና ራዱ።

9. ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ከውስጡም ፍሙ ጋለ።

10. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

11. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

12. ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።

2 ሳሙኤል 22