2 ሳሙኤል 22:36-41 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።

37. እርምጃዬን አሰፋህ፤እግሮቼም አልተሰነካከሉም።

38. “ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤እስኪደመሰሱም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።

39. ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።

40. ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከካቸው።

41. ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው።ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው።

2 ሳሙኤል 22