19. በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፈኝ።
20. ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።
21. “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤እንደ እጄም ንጹሕነት ብድራትን ከፈለኝ፤
22. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ከአምላኬም ዘወር ብዬ ክፉ ነገር አላደረግሁም።
23. ሕጉ ሁሉ በፊቴ ነው፤ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።
24. በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።
25. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ።
26. “ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ መሆንህን፣ለቅን ሰው አንተም ቅን መሆንህን ታሳያለህ።
27. ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።