2 ሳሙኤል 22:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤

2. እንዲህም አለ፤“እግዚአብሔር ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤

3. አምላኬ፣ የምጠጋበት ዐለቴ፣ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው።እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ከኀይለኞች ሰዎች ታድነኛለህ።

2 ሳሙኤል 22