1 ጴጥሮስ 2:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ምክንያቱም በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤“እነሆ፤ የተመረጠና ክቡር የማእዘን ድንጋይ፣በጽዮን አኖራለሁ፤በእርሱም የሚያምን፣ ከቶ አያፍርም።”

7. እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን፣“ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።”

8. ደግሞም፣ “ሰዎችን የሚያሰናክል፣የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ።”የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።

9. እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ሕዝብ ናችሁ።

1 ጴጥሮስ 2