1 ዜና መዋዕል 29:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይናበምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።

12. ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው።

13. አምላካችን ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።

1 ዜና መዋዕል 29