1 ዜና መዋዕል 26:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤ በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፣ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ጊዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።

18. በምዕራቡ በኩል የሚገኘውን አደባባይ ደግሞ በመንገዱ ላይ አራት፣ በአደባባዩ ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።

19. እንግዲህ የቆሬና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድል ይህ ነበር።

20. ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

1 ዜና መዋዕል 26