1 ዜና መዋዕል 24:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደሚከተለው ነበረ፤የአሮን ልጆች ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር ነበሩ።

2. ናዳብና አብዩድ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።

3. ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው።

1 ዜና መዋዕል 24