1 ዜና መዋዕል 23:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።

13. የእንበረም ወንዶች ልጆች፤አሮን፣ ሙሴ።አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።

14. የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15. የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ጌርሳም፣ አልዓዛር።

1 ዜና መዋዕል 23