6. ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
7. ከጌድሶን ዘሮች፣አለቃውን ኢዮኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
8. ከኤሊጻፋን ዘሮች፣አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
9. ከኬብሮን ዘሮች፣አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
10. ከዑዝኤል ዘሮች፣አለቃውን አሚናዳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
11. ከዚያም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ ዓሣያን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያን፣ ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣