8. ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተው የእርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ እነርሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ፊታቸው እንደ አንበሳ ፊት የሚያስፈራና በየተራራውም ላይ እንደሚዘል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
9. የእነዚህም አለቃ ዔጼር ነበረ፤ሁለተኛው አዛዥ አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣
10. አራተኛው መስመና፣ አምስተኛው ኤርምያስ፣
11. ስድስተኛው ዓታይ፣ ሰባተኛው ኢሊኤል፣
12. ስምንተኛው ዮሐናን፣ ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣
13. ዐሥረኛው ኤርምያስ፣ ዐሥራ አንደኛው መክበናይ።
14. እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ ከእነርሱ ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺህ አለቃ ይቈጠር ነበር።
15. በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ፣ ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።