1 ዜና መዋዕል 11:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።

16. በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ደግሞ በቤተልሔም ነበረ።

17. ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣ “ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

18. በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጒድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤

1 ዜና መዋዕል 11