1 ነገሥት 9:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር፣ በኤሎት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።

27. በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋር አብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ።

28. እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ለንጉሥ ሰሎሞን ሰጡት።

1 ነገሥት 9