1 ነገሥት 4:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤

2. ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤

3. የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍናአኪያ፣ ጸሓፊዎች፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤

4. የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤

5. የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃገዦች የበላይ ኀላፊ፤የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡየቅርብ አማካሪ፤

1 ነገሥት 4