1 ነገሥት 1:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ንጉሥ ዳዊት እየሸመገለና ዕድሜው በጣም እየገፋ ሲሄድ፣ ልብስ ቢደራርቡለትም እንኳ ሊሞቀው አልቻለም።

2. ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ “ንጉሡን የምትንከባከብና የምታገለግል ወጣት ድንግል እንፈልግ፤ እርሷም ጌታችን ንጉሡ እንዲሞቀው በጐኑ ትተኛለች” አሉት።

3. ከዚያም በመላው እስራኤል ቈንጆ ልጃገረድ ፈልገው ሱነማዊቷን አቢሳን አገኙ፤ ለንጉሡም አመጡለት።

1 ነገሥት 1