1 ተሰሎንቄ 5:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እግዚአብሔር ድነትን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንድናገኝ ነው እንጂ ለቍጣ ወስኖ አላስቀመጠንምና።

10. ብንነቃም ሆነ ብናንቀላፋ ከእርሱ ጋር በሕይወት እንድንኖር እርሱ ስለ እኛ ሞተ።

11. ስለዚህ በርግጥ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፤ አንዱም ሌላውን ያንጽ።

1 ተሰሎንቄ 5