1 ተሰሎንቄ 1:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤የእግዚአብሔር አብና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

2. በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን።

3. ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።

1 ተሰሎንቄ 1