1 ቆሮንቶስ 4:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለ ዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል።

2. ባለ ዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።

3. በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም፤ እኔ እንኳ በራሴ ላይ አልፈርድም።

4. ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ይህ ግን ጥፋት አልባ መሆኔን አያረጋግጥም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው።

1 ቆሮንቶስ 4