1 ቆሮንቶስ 12:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቦአል።

19. ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር?

20. እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው።

21. ዐይን እጅን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም።

1 ቆሮንቶስ 12