1 ቆሮንቶስ 10:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከእርሱ እንበልጣለንን?

23. “ሁሉ ነገር ተፈቅዶአል”፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉም ነገር ተፈቅዶአል”፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር አያን ጽም።

24. እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ የራሱን ብቻ አይፈልግ።

25. በኅሊና ምርምር ውስጥ ሳትገቡ፣ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ብሉ፤

26. ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።

1 ቆሮንቶስ 10