1 ሳሙኤል 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤“ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤በማዳንህ ደስ ይለኛልና።

2. “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።

3. “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።

1 ሳሙኤል 2